እሷኮ
እንደው እሷ ማናት ብለው ቢጠይቁኝ እኔም እንዲህ አልኩኝ እሷማ እናት ናት ፍቅሯ የፀና አለት እንደ ፀሀይ ውበት እንደ ክዋክብት ድምቀት እንደ ጨረቃ ፍክት ብላ የደመቀች እሷኮ ፍቅር ነች ደግሞ ቀጠልኩና እሷማ ምስጢር ነች ከሰማይ የራቀች ከውቅያኖስ የጠለቀች ከጥላቻ የራቀች በትሕትና የተሞላች እሷማ ፍቅር ነች ደግሞ ቀጠልኩና እሱም የመላዕክት እህት የአሕዛብ እናት ድንግል ማርያም ናት
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
