ምናልባት
ከእለታት አንድ ቀን ተክዤ ስራመድ ትልቅ ምሁር አባት አገኙኝ በመንገድ በትሁት አንደበት ልጄ ሆይ እንዴት ነሽ ቀናም አልኩ አየዃቸው ደገሙት ደና ነሽ እራሴን ጠየኩ ማን ቢነግራቸው የውስጤን መረበሽ ቀጠሉ ልጄ ሆይ ወዴት ትሄጃለሽ ድንገት ቃል አወጣሁ ልፈልግ ለጥያቄዎቼ ምላሽ ልምከርሽ አሉና ብለውኝ ምናልባት ባታውቂኝም እንኳ አድምጪኝ እንደ አባት አይኖርም አይባል ማንም ካልተማረ በስብዕናው እንጂ ሁሉም የከበረ አልጠፋም የሚሠራው አጥቶ የዋለለ እግዜር የከፈተውን መች ሳይዘጋ ዋለ ዛሬ ላይ ያገኘ ነገን እንደሚያጣ ጭራሽ ባያገኝስ ደግሞ ምን ሊያመጣ የሕይወት ቅመሙ ተመስገን እያለ ራሱን ለማጠንከር ሊሆንም ላይሆንም ካላለ ማውጣት ማውረዱ መቁጠር የጎደለ ሀሳብን በልኩ ምናልባት አለመኖር አለ ልክ እንደዚ ሲሉ ነቃሁኝ ከእንቅልፌ በምስጋና ሸኘሁ እራሴን ነቅፌ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
