አንድ ቀን
ናፍቆት በረዘመ ምኞት በገዘፈ ድካም በበረታ ሁሉም ልክ ያለፈ ህይወት ሚስጥራዊ አለ የተፃፈ የስሜቶች መድከም የልብ ስብርባሪ ሀኪም የማይፈታው ካልሆነ ፈጣሪ ጭንቀት ሀብት ደስታ ሁሉም ሊሆን ቀሪ አትኑር ለሰዎች አትፈልግ ምስጋና የሰማይ አባት ነው የሚያደርገው ቀና የማይክድ የ እውነት አፍቃሪ ነውና ገናና ልብ ልቡን ያምናል አይንም ራሱን ያምናል አእምሮውንም የሳተ ሰው እንዴት ይሆናል በራስ እንቆቅልሽ ካሉ እኔ ማነኝ አይቀር ተደብቆ መሄድ ወደ አፋልጉኝ ቆም ብለህ አስብ ይህን ሁሉ ሁካታ ሞቅታ አበቃ የህይወት ደምስርህ ሲበጠስ ለአፍታ ምድር አስጨንቃህ ሞትን ብትመኘው አባብሎህ ይመጣል ያያያ አንድ ቀን እሱ ነው ታድያ በዛ ጊዜ ለነፍስ ያላዘነ ለስጋህ ያለቅሳል ተግባራቸው ይመስል እንቅልፍ ሞት ያስንቃል እስትንፋስ እስካለህ ይኖራል ሁሉም ያፈራኸው ህይወትን አደራ ለማን ልትሰጠው ነው በከንቱ መጨነቅ ያለ አቅም ደስታ ያለው በሰማይ ቤት ነው ዘላቂ እፎይታ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
