ማን ነው?
ጥፋት ጥፋት ገኖ እራሱን አጋኖ፣ ለወንጀል ማንነት እራሱ ወግኖ፣ ፍርደኛው ጠፋበት እራሱ ፈትኖ። ሚዛኑ ከደፋ ወንጀል ካጋደለ፣ ወንጀለኛው ገኖ ሕሊና በደለ። ፈረስ ካመረረ እርግጫ ካበዛ፣ እንዲሁ አይፈካም የአበባ መአዛ። ቢሰራ ቢተረክ ቢደረግ ክወና፣ ታሪክ ቢጻፍለት ቢኖረው ፈተና፣ ፊልመኛው ብዙ ነው የወንጀል ገመና፣ ለካ ድራማ ነች አለም እንደገና። ሙስና ወንጀል ነው ተብለን ተምረናል፣ አስተማሪው ብሶ ሲሰጠው አይተናል፣ አንድ ሣንቲም ናቸው ቢሉን ይሻለናል። _______:___:______:___
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
