ህይወት ሻማ
ህይወት እንደሻማ ታበራለችና ግን እንዲሁ አትቀርም መቅለጧ ነውና ከአላማህ ስትደርስ ብለህ ደፋ ቀና ታድያ እስከመቼ ራስህን አዝናና ተሰባሪ እንጨት አንተም ሰው ነህና መልካም ሁን እስካለህ በምድር ግድ የለም አሸንፍ ጥላቻን በፍቅር ይገባሃል ደስታ ይገባሃል ክብር ስንት ፈተና አለፍክ የዛሬን ለማደር ይብዛልህ ሰላሙ ደስታህ ደስታዬ ነው ሁሉም ትርጉም ያለው አንተ ስላለህ ነው ምን ብትቀያየር ህይወት ዘመናይት እንዳታጨልምህ ከቶ ፊት አትስጣት።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
