እናቴ
ስምሽ የገነነው እንዲህ በአለም ለገርም ተጠራች ይኸው ባንቺ ስም አምሳያ የሌለሽ ጨርሶ መተኪያ ከሁሉም ተመርጠሽ ለፍቅር መለኪያ ልጆችሽ ሲጠሩሽ ሲሉሽ እማ እማ አንጀቴ ይርሳል ሰምሽን ስሰማ ፍቅርሽን ለግሰሽ የእናትነትሽን መች ይሆን ምላሹ ይህ ውለታሽን አለም በሞላ ህዝብ ብኖር ተከብቤ ካንቺ ውጪ አይሻም መቼም ቢሆን ልቤ የውጤ አዳማጭ ጓዳና ሚስጥሬ ድሮስ በማን ሆነ እንዲህ መከበሬ ምስጋናም ቢያንስሽ ህልሜ ግን እሩቅ ነው ሀሳቤማ ላንቺ ገና ተራራ ነው ሁሌም ምለምነው አምላኬ ምኞቴ ያሰብኩት ተሳክቶ እስካለች ህይወቴ ውለታሽ በዝቶብኝ ከፍዬም ባልጨርሰው በቃ ቃል የለኝም እድሜሽን ያርዝመው።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
