ስለምን
ሀሴትን አየዃት በዛሬዋ ቀኔ አንድ እርምጃ ቀጠልኩ በሒይወት ዘመኔ የዛሬዋ ቀን ደስታ እስከ ነገ ድረስ ክፋትን ጠላሁት ዳግም ላይመለስ ቃል ገብቻለሁ ላላይ ወደ ዃላ ማንስ ሊያበረታኝ እኔን ከኔ ሌላ ፍቅርን አገኘዋለሁ በሄድኩበት ቦታ መለየት እስኪያቅተኝ ሀሰት ይሁን እውነታ የኔ ነሽ እያለ ቀን መሽቶ እስኪነጋ ሆኖብኝ እንቅፋት እኔን ሊያዘናጋ ከኔ ቢውል ዛሬ የልቡ እስኪደርስ ቀን ጥሎኝ ስሸነፍ ሄዷል ላይመለስ ወደድኩሽ የሚለው ልቡ እስኪሰበር ፍቅርን ላይጨርሰው በቃላት መደርደር በዚም ሌላ ወሬ የሰዎች ጋጋታ ሀሳብን ማስፈሩ ባልዋሉበት ቦታ እውነትን መርጬ ካልሆነ ዝምታ ብዙውን ሰምቼ ላልቀድም አንድ እርምጃ ለሁሉም መፍትሔ ጊዜ ነው ማስረጃ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
