ሳይሰማ ጥሩልኝ
ከብዙ ሴቶች ርቆ እኔን ይቀርበኛል ታድያ እንዴት ለምን ጠላሁሽ ይለኛል አንድም ተስፋ ሰጥቶ አንድም ይጎዳኛል እኔስ ግራ ገባኝ መንታ ሆኖብኛል ፍቅሩ እያበነነኝ እንደ እፉዬ ገላ ሲያሳስቅ ወስዶ ሳያዞር ወደ ዃላ አይ አትፈታ አንተ እንቆቅልሽ ገና ሳስብ አንተን የልቤስ መረበሽ በቃ ሄደ እንዳልል ይመጣል ቆይቶ በመምጣቱ ልቤን ደስታ ሞልቶ ደሞ ይመለሳል አንጀቴን አብላልቶ ያንተ መሄድ መምጣት የኔስ ልብ ስቅላት የናፈኩህ ብዙ ቢሆንም ለአመታት ላንተ የኖረች ነብሴን ጠላሁሽ አትብላት ንገሩት ከሰማ ብቅ ብሎም ካየኝ ሳይሰማ ጥሩልኝ ደሞ እንዳይቀየመኝ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
