ፍቅር
ፍቅር ደስታዬ ነው ፍቅር መጽናኛዬ ምን አለ ባገኘው ሆኖ የብቻዬ በቀለም ጠብታ በወረቀት አስፍሬ ባልጨርሰው እንኳን ሰፍሬ ሰፍሬ ቃላትን ባጣለት ሆኖ ጣፋጭ ፍሬ ምሎ ላይለቀኝ ገብቷል ከደም ስሬ በከዋክብት ፈገግታ በጨለማ ላይ ብርን ተገልጦ እስካይህ የአይኖቼ ሽፋን ሳልነግርህ የምትረዳው የልቤ ትርታን ይህ ፍቅርህ እኮ ነው የሚሰጠኝ ተስፋን ፍቅርን ያስመሰክር የሰው ማንነቱ እጅ ወደላይ እንጂ ያበራል ከፊቱ ከመራኝ መንገዱን ልሂድ ተከትዬ ለጥላዬም አልዞር ሁሉን በሱ ጥዬ ይከፍለኝ እንደሆን የጣልኩት እምነቴ ከ እንቅፋት ሸሽጎ ያደድርሰኝ ከቤቴ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
