ህይወት ቢራቢሮ
ህይወት ቢራቢሮ አይነቷ የበዛ ከለሯ የፈካ አንዳንዴም ደብዛዛ ብትከብድ ብትቀልም እንደተቀባዩ መንገድ አይቋረጥ ግራ ቀኝ ሳያዩ ምንድነው መሟገት ላይቀር ውጣውረድ አመስግን በተራህ ሳታይም አትፍረድ ይባላል ሲበዛ ማርም የሚመረው ምድር የምትከፍልህ እጣፋንታህን ነው ሲጨልም ሲነጋ ቀንን የምንቆጥረው በእንባ ሀዘን በደስታ ፈገግታን የምናጣጥመው ለአንዱ እየጎደለ ለሌላው ሲሞላ ልባችን ይደንድን ሁሉም ላይሆን ተድላ እንዳሞራ ወደላይ በሰማይ መክነፉ እንዳንቀር ተንሳፈን እንደካደው ክንፉ መንገዷ ቢረዝም ባይታወቅ ፍፁሟ ብዙ ነው እንደቢራቢሮ የህይወት ቀለሟ ለኔ የደመቀው አንተ ላይ ቢፈዝም ሁሉን የሚችለው ዝም አይነቅዝም ስትጀምር አይተህ ቻልበት መብረሩን ከ እሾህ እንዳታርፍ ምረጥ አቅጣጫውን።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
