ዝምታ
ምርጫዬ አድርጌ ዝምታን ባሰላ ይመሰክር ጀመር እሱም እያደላ የእውነት መንገድ እንጂ መች ጠፍቶኝ ማውራቱ እንደ ወንዝ ዥረት ቢሆን የቃላት ብዛቱ ትርጉም የለሽ ድካም ትርፍ የሌለው ወሬ ቃል ካጣ ቦታውን ዝምታ ነው ክብሬ ተከሳሽ እንዳለው ጠበቃና ዋሴ አይወጣኝም ትንፋሽ ዝምታ ነው መልሴ አለመቻል አሉት የዝምታን ወጉ በወረት ተሸኘ የጉብዝና ደጉ ተከሳሽ በውሸት ወንጀለኛ ፈሪ አንተው ጥፋተኛ ደግሞም አጭበርባሪ ዝምታን የዋጠ ቢያደርጉ አስመሳይ ሆኖ ባለመቅረብ የእነሱ ተካፋይ የበደል ቆጠራው እኔ ላይ ቢከመር የማልፍበት የለኝ ከዝምታ በቀር መናገር መሻትህን አይንህ ቢያሳብቅ ሃቅ እስክትቀርብህ በዝምታ ተደበቅ ዝም በል አትናገር ምን አሉኝ ብለህም አትቁጠር ላንተስ ምን ተርፏቸው ፈጣሪን ሰቅለውት በምድር።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
