ሽ....!!!
አንድ ሰው ገረመኝ ብዙ ከማውቃቸው በጥቂቱም ቢሆን እስኪ ላካፍላቸው አንደበቱ ቁጥብ ሁሌም ተፈላጊ ደግነቱ የበዛ ቁጣው አስበርጋጊ እውነት የታጠቀ ብሎም ታማኝነት አቤት አፈጣጠር ታድሎ ወንድነት ለሁሉም ምሳሌ ቀዳሚ ከቤቱ በአባቱ ተጠሪ ጀግና ነው ለእናቱ ለጠላት ብልህ ጦር ለወገኑ ጋሻ ትዕግሥት መሳርያው ለጊዜ ድል መንሻ እንቅፋት ያልጣለው ጎነ ጥንካሬ ከአሳቡ ያልገባ ምን ወለደ በሬ ከልቡ የሚወድ የሁሉ አክባሪ ለእናቱ ታዛዥ ሀይማኖቱን ፈሪ በግርማ ሞገሱ ሆኖ የሰው ልዩ ለአይን እንኳን አይሞሉ ከእሱ አንፃር ሲታዩ ምላሹን አገኘሁ ይግደል የተማረ ሁሉ የተዋጣለት ራሱን የስከበረ ችሎ የማይገልፀው የቃላት ጋጋታ አምላክ የፈጠረው ለቤተሰቡ አለኝታ በምን የታደለ ከማን የዘረፈው ዘሩን አጣሩልኝ ማን እንዳወረሰው።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
