አየዃት ያቺን ልጅ
አየዃት ያቺን ልጅ ልቤ ደነገጠ ካጠገቧ ስደርስ ሀሳቤ ተዋጠ የልቤን ትርታ ሳልነግራት ደፍሬ እርበተበታለው ይኸው እስከዛሬ መነመነኝ ፍቅሯ ገብቶ በደም ስሬ ምን ሆነሃል ቢሉኝ በፍቅሯ ታስሬ አፍ የሌለው ሆኖ አስሮኛል ጠፍሮ እሷኑ ስከተል ከአስፋልት እስከ ጓሮ ከዛሬ ነገ ገብቷት ይሆን ብዬ እሹሩሩ እያልኩ ሳወራት አባብዬ እኔው ግራ ገብቶኝ ምኗ እንደሰረቀኝ ጥላዋ መስዬ ከስሯ የምገኝ ፍቅሯ ሊጥለኝ ነው ይኸው አደናብሮ ከሷ ውጪ ሀሳብ አወይ ጉድ ዘንድሮ ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
