አይ ሰው
መልካምና ደግ አምላክ ምስጋና ይድረሰው በከአሊነቱ በምድር የሚኖር ሰውን ለፈጠረው የፍጥረታት ጌታ ሩህሩህ የሁሉ ቸር አባት ፍቅሩ ያለሚዛን ገደብ የለሽ ምህረት ታሪኩ የበዛ ሁለት ፊደላት ሰው እንደስሙ ቢቀል ታድያ ምን አነሰው በገዛ ስልጣኑ እራሱን ያነግሳል እሱ ብቻ አዋቂ ሌላው ይሳሳታል የፈጠረህ ይመስል አይምሮህን ያነባል ካፍህ ቃል ሳይወጣ ሁሉን ባንተ ይፈርዳል ቢሆን የሞት ፍርዱ በእጅ ስልጣኑ ቀን ባጠረ ነበር ወገን ለወገኑ ልቡ እንደ ድንጋይ ጠፍቶ ሀዘኔታ ከቶ ዋጋም የለህ እንደሱ እይታ እንደ አህያ ጎብጠህ እንደምንጣፍ ደቀህ ብታገለግለው ምስጋናው ቀርቶብህ የእድሜ ልክ ባርያው ብትሆን ደስታው ነው ውስጥህ እየደማ አንደበትህ ቃል ቢያጥረው ሀይልን መሰብሰብያ ድክመትህ ድሉ ነው ሲያሻው ከዙፋኑ በላይ ሲለው ከእግሩ በታች ከሁሉም ይነጥቃል ማን ሊለው የበታች ለመወደስ ብሎ አንዱን የቀበረ ላይሆን እንደሰው በእግዜር የከበረ ላይምርህ አትታይ በልጠህ ከተገኘህ የሚያሳድድህ ትልቅ ጠላቱ ነህ ተው ይቅርብህ ከእጁም አትብላ ደሞ የከፋው ቀን ሊልህ አፈር ብላ የሰውን በሀሪ መግለፁም ቢከብደኝ ብዬ ተመኘሁ ዝምታን በዋጥኩኝ ታድያ ይፈረዳል ሰይጣን ቢቀናበት ሁሉን አጠናቆ በልጦ ተገኝቶለት ቆሜ መራመዴ መች እንደሰው ሆነና እንደርሱ ፍቃድ እንጂ ቢያንሰውም ምስጋና የሰው ትርጉሙ ቢጠፋኝ ምንድነው በደሉ የበዛ የክፋት ጥግ ነው።
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
