ስናፍቅሽ
ሰኞ እለት አግኝቼሽ ማክሰኞ ናፈቅሽኝ ለ እሮብ ቀጥሬሽ ሀሙስም የለሽም ለ አርብ ጠብቄሽ ቅዳሜም ቀጣሽኝ እሁድም ባሰብኝ ቀኑም ረዘመብኝ ሳምንቱ ወራት እስኪመስለኝ ለ አመት ብለይሽ ደሞ ምን ሊውጠኝ ከ እቅፌ አትውጪ ሁኝልኝ ከጎኔ ፈልጌ አልጣሽ ሁኚ ሰመመኔ አንቺን በመጠበቅ ቢደበዝዝ እንኳን የአይኔ ብርሀን ተስፋን የምሞላው ቢሆንም ጨለማ ቢጠፋም ወጋገን መች ይሆን እረፍቴ ሆነሽ ከኔ ወገን ግና ምን አስችሎሽ እንደኔ ከሆነ ሀሳብሽ ነው እኔ ብቻ ነኝ ሁሌም የማስብሽ አቅም የነጠቀኝ የጣለኝ ናፍቆትሽ ስምሽን ዘንግቼ አልኩኝ ስናፍቅሽ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
