የእኔ ሌባ
ኡኡታዬን ስሙ ቅሬታ አቅርቤያለው አያድን አልሰማሁ ሁሉም ተከሳሽ ነው መተኪያ የሌለው ንብረት ተነጥቄ ይመልስ እንደሆን እንዲህ ማስጠንቀቄ አቅም ሳይኖር ዳገት መሞከር ተራራ ጉልበት የከዳው ሰው ይታይ ጎበዝ አውራ ሳይቀር ለ አሻራ ማነው የዘረፈኝ አጣሁ መዳረሻ ወዴትስ ደበቀኝ መልኬ ጠፍቶብኛል ሌላ ሰው ሆኛለሁ በጭንቀት መረብ ውስጥ ራሴንም ጥያለሁ አመሌም የከፋው ስፈልገው ራቀኝ አጥብቦ በማሰብ ሰፊው አለም ጠበበኝ አልችልም ስንፍናን በራሴ ላይ ሾሜ ተስፋን በማሳጠር እንባ ተሸልሜ ሰርቀው ምን አደረጉሽ የሳሳሽው ልቤ እንዲህ የጨከንሽው ተጣልተሽ ከ ቀልቤ ያለ አንቺ ማን አለኝ ለስጋዬ እዘኚ ፈጣሪሽን ፍሪ ለክፋት አትተኚ ድካሜ ቢበዛ አዘንኩ ለራሴ ነይ ተመለሺ የዘረፉሽ ነፍሴ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
