ተስፋ ይኑርህ
ልብ ያለው ልብ ይበል ላልሰማም ያሰማ ህይወት አንዳንዴ ብትሆንም ጨለማ መብራቱን ብታጣ ደሞ አለ ሻማ ምንም ቢበረታ ዳገት ቁልቁለቱ ገደብ የለሽ ቢሆን የልብህ ፍርሃቱ ባይዘንብ ያካፋልኝ አይደለም ተረቱ አምላክ የፈጠረን አይደለም በከንቱ ዛሬን እየቃኘህ ነገን ልትፍቃት የመኖርን ትርጉም ተስፋ ነው የሞላት ዛሬን ብትስቅ እንኳን ጥርሰህ እስኪደክመው ግን እንባህ አይራቅ ነገን መች አየነው የፀሃይዋ እህት ትንሿ ጨረቃ አላየህም እንዴ በአለም ላይ ደምቃ ቀኑን በዝምታ ስታልፍ ተደብቃ ለካስ እስኪመሽ ነው ቦታዋን ጠብቃ ምድርን ያደመቀች በብልሃት አንፀባርቃ ሰው ሆይ ሁን እንደጨረቃ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
