ልግጠም
ኧረ ልግጠም በሌለህ ጀግንነት እንዴት ትገጥማለህ ያንተ መክሊት ሌላ ከላይ የተሠጠህ ብሎ ይመክረኛል ይለኛል ያስጠነቅቀኛል ይለኛል ጓደኛ ይለኛል ዘመዱ እንደኔ ባይከፋው ባይጨስበት ሆዱ ልቡ ከሻከረ ወንድ ልጅ ከከፋው ይገጥማል'ንጅ ገብቶ ከጫካው ብሶቴን እያሰብኩ ተስፋየን እያለምኩ እኔስ እገጥማለሁ ወደ ጫካ ሄጀ ድቡን ተንተርሸ ተመርኩዠ በ'ጀ ስንቅና ትጥቅ አልል መች አስቸግራለሁ ባይደላኝ ነው እንጅ ግጥም ልግጠም ብየ የቆምኩት ከደጅ። አጣጣል ባልችልም ባይለምድም ብዕሬ እገጥማለሁኝ ልክ እንዳጅሬ መጋቢት 10/2015 #Kibkab Wondossen
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
