ጭር ካለው ስፍራ
ሳወጣና ሳወርድ ውሎና አዳሬን ከፍ ዝቅ ማለቱ ከንቱ መባከኔን እራሴን አጥቼ ሃሳብ ተሰርቄ ውሳኔ ሸሽቶኛል ሁሉንም መርቄ በዚህ ሲሉት በዚያ ከቶ ማይጨበጥ ተስፋ ቢያስቆረጠኝ ተባልኩልሽ ቀበጥ ለማን ባስረዳው ነው የውስጤን ጨለማ የምኖር ለሌላው የምኖር ነፍሱን እንደተቀማ ፍቅር ያሸንፋል ሲሉ ሰምቻለው ሰላሜን ያሳጣኝ ታድያ እኔን ብቻ ነው ዝምታ ወርቅ ነው መባሉም ልክ ነው ለሚተገብረው ትልቁ ወንጀል ነው አእምሮዬም ዛለ ልቤም ተዳከመ እንደኔማ ሃሳብ ሁሉም ተፈፀመ እኔን የሚገርመኝ የምድር ክፋቷ እኩልነት አታውቅ ጭራሽ ማዳላቷ ምኞት መቼ ራቀኝ መሆን ልበ ቀና በዝቶ እራስ ወዳድ በሰፊው ጎዳና።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
