እናቴ
ስምሽ የገነነው እንዲህ በአለም አገርም ተጠራች ይኸው ባንቺ ስም አምሳያ የሌለሽ ጨርሶ መተኪያ ከሁሉም ተመርጠሽ ለፍቅር መለኪያ ልጆችሽ ሲጠሩሽ ሲሉሽ እማ እማ አንጀቴ ይርሳል ስሞሽን ስሰማ ፍቅርሽን ለግሰሽ የእናትነትሽን ከክብርሸ ዝቅ ብለሽ አኛን ያሳደግሽን አለም በሞላ ህዝብ ብኖሮ ተከብቤ ካንቺ ውጪ አይሻም መቼም ቢሆን ልቤ የውስጤ ጓደኛ ጓዳና ሚስጥሬ ድሮስ በማን ሆነ እንዲህ መከበሬ የስሜ መነሻ የመጨረሻ ፍቅሬ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
