ይቅርታ!
ከፍጥረታት ባህሪ በልጦ የነገሰ የጨዋነት ምስክር ይቅርን ተላበሰ ይቅር አያሳስብህ መውደቅ መዋረዱ በአንድ ቃል ማሸነፍ ክምር ከመናዱ ማነው የፈቀደው ብቻ ለበደለ በምድር ነጋሹ ይቅርን የታደለ እንዴት ያለ ፀጋ ለመከበር ማነስ ቅንጣት ሳይበድሉ በቅጣት መከሰስ ብትዘገይ እንኳ የእውነት ዳኝነቷ ከሀዲ ብታስብል አይቀርም መምጣቷ አያስጥል ከክፉ ሽንጥ ይዞ መገተር ትልቅ ነኝ ካልክማ አንገትህን አቀርቅር ባይሆን ምርጫህ ይሁን የ ትዕግሥት ጓደኛ ማለፍን ያስተምርህ ከሁሉም ምቀኛ ከብልጠትም ታረቅ እንዳትሆን ብቸኛ በ አንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ያድርግህ ዘዴኛ ከሰላም ቤት ግባ ሕይወትህ እንዲቃና የዘወትር መገኛ ዙፋንህ ነውና ፍቅርን ለማበልፀግ በሕይወት መንገድ ሆነህ ስትገኝ ነዉ የ ይቅርታ ዘመድ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
