እሞት ይሆን
እዚህ ምድር ኖሬ ካለሁበት ድረስ፣ አስካለሁ የኖርኩበት ባላገኝ ሠላም ፈውስ፣ እስካሁን አለሁኝ አለም ስትፈራርስ። መጨረሻ ሆኖ እድል እጣ ፈንታ፣ አፈሩ ቢቀለኝ ከላይ ባገኝ ቦታ፣ ደስ ብሎኝ ባርፍ ነው ባስበውም ላፍታ። ሠው መሰድር ኖሮ አፈር ለሚበላው፣ የራሱ በሽታ እራሱ ሲገለው፣ ለመኖር ቢለፋ ሞቱን ላያስቀረው። ገነሰዘብ ምን ጠቀመው ለምድሩ አፈር፣ ሠው ሆኖ ተፈጥሮ በሞት ለሚሠበር። አስበው ነበረ ይህን ጊዜ ላፍታ፣ እኔው ፍጡሩ ነኝ የምድር ከርታታ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
