ልቤ ግን
ይበራል ይጠፋል ታሞም ይድናል ይወድቃል ይነሳል ተስፋን ይጨብጣል ለጠላው ግድ የለሽ ለወደደው ሟች ነው ግን ደሞ ቀልድ የለም ታማኝ አፍቃሪ ነው ልቤ ግን ጎበዝ ነው ሁሉንም ይችላል አማኝም ታማኝም ለቀረበው ሁሉ ውስጡ የገባውን ላይተው በቀላሉ ልቤ ግን ጎበዝ ነው እኔ አደንቀዋለው ለመጣው ብሎ well come ለሄደው well go ነው እንዲ አይነት ልብ ያለው ታድያ እድለኛ ነው እንደ አመጣጥ መቀበል ታላቅ ችሎታ ነው እንግዳ አሸኛኘቱም እንደ ባህላችን ነው ልቤ ግን ጎበዝ ነው እኮራበታለው ያከበረውን ያውቃል የናቀውን ይርቃል ሰውን ላያስቀይም ቀድሞ ይጠነቀቃል በችራሽ አይፈራም ክብሩን ይጠብቃል እንደኔ አይቸኩልም ለሁሉም አለው ቃል ልቤ ግን ጎበዝ ነው ሁሉን ነገር ያውቃል።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
