ቀረህ አይደል
ልቤን የወሰድከው ባማሩ ቀለማት ሕይወቴ ነሽ ያልከኝ በተዋቡ ቃላት ስላመንኩሕ ይሆን የሆንክብኝ ጠላት ብለኽኝ ነበረ አሎድም ውሸታም ምነው የሸለምከኝ የክሕደት አለም ቃላት እስኪጠፋህ ብለህ ማሬ ማሬ መለየት ሆነ እንዴ የፍቅርህ ጅማሬ እመጣለው እያልክ እንደወጣህ ቀረህ ልቤም አንተን ብሎ እንደኮበለለ ማን በነገረህ በጭላንጭል ተስፋ ውስጤን የማሞኘው ትመጣለህ እያልኩ መንገድ የምቃኘው ካላየሁት ብዬ ሞቴን የምመኘው ደና ነኝ አልልም አሞኛል በብዙ እንዳልሆን አድርጎኝ የፍቅርህ መዘዙ አንተን በመጠበቅ ራሴን ተሰርቄ ጉንጬ እንደረጠበ መች አውቅና ስቄ ጨርሶ ማይደክመኝ ዳገት ቁልቁለቱ ቢቀልልኝ ብዬ የናፍቆት ብዛቱ ወጣሁ ወረድኩ እንዲሁ በከንቱ ያኔ ቃል ስትገባ ብለህ ግራ ጎኔ አሁን ግን የለህም ስናፍቅህ ለአይኔ ዛሬ ነገ ሰትል ወራት አልፈው አመታት ተቆጥረው እመጣለሁ አልከኝ ዛሬም እንደድሮው ምናል ባደረገኝ የግርህ መረገጫ በሄድክበት ሆኜ ለናፍቆት መወጫ ሁለት ልብ አድርገህ ወይ ላትቀር ላትመጣ ከየትኛው ልሁን አወይ የኔ እጣ ወላጆቼ ቢሉኝ ተይው ተይው በቃ ጓደኞቼም ሲሉ ኸረ ተይው በቃ በቀላል የሚተው መስሏቸው እቃቃ እኔው ተዉኝ አልኩ ከእንቅልፌ አሰክነቃ ብቅ ብትል እንኳን ድንገት ሳላስበው ልጠብቅህ አይደል አንተ የልቤ ሰው።
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
