ሚስጥራዊው ፍቅሬ
አይኔ ላይ ውል ቢል በአንድ አጋጣሚ አየሁት ለመድኩት በተደጋጋሚ ገና ባንድ ዕይታ ለሱ መረበሼ ሱሴ ሆኖ አረፈ አልበጀ መሸሼ ንግግር ቁመናው ሁሉ የሚያስቀና ታተመ ልቤ ላይ ምርጫዬ ሆነና ታድያ እስከዛሬ አይኔን ያማተርኩት ከሁሉ አብልጬ ወድጄው አረፍኩት እንዴት ብዬ ልግለፅ የልቤን ድምታ ያሳብቅ የለም ወይ ከበሮ ሲመታ ፍቅር ወይስ ልክፍት እኔስ ያገኘሁት አይኑን ለማየት ድፍረትን ያጣሁት ሰምቶ ይሆን ብዬ የምሸማቀቀው ለማንስ አውርቼ ልቤስ መች አወቀው ቀረ እንጂ ታፍኖ ውስጤን እያሞቀው አይደለም አስቤ አስሬ ቢታለም ጎልተህ የምትታይ ብትሸፍንህ አለም አድማጭ በሌለበት የውስጥ አማካሪ ወሬው መቼ ጠፋኝ በዝቶ እንጂ ፎጋሪ የሰው ፍጡር ሆነ አይ እንዳልዋሰው ቢናፍቀኝ አይደል በአይነ ህሊና የማመላልሰው ቃላት ሀይል የላቸዉ እሱን ማወደሻ አጣሁ ብፈልግ ለክብሩ እጅ መንሻ ንብ የምትቀናበት በታታሪነቱ ልዩ አድርጎታል ሰው አክባሪነቱ ህልም ነው እያልኩ ዋሸሁት እራሴን ውስጤ ተመርዞ እንዳላጣው ነብሴን ሳላውቅ የወደድኩህ ሚስጥራዊው ፍቅሬ ይቅርታን ተቀበል ከጎኔም አትራቅ የሕይወት መነፅሬ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
