በራስ ማበድ
በቆምኩበት መንገዳገድ በሄድኩበት መወላገድ ምን ይሉታል ይህን መንገድ እራሴን ካጣሁት አውቆ እንዳበደ ህይወት ተበላሸ ነገሩም ነደደ አመሌም ቢከፋ መልኬም ቢጠፋብኝ ያ የምሳሳለት ፊቴም ረጠበብኝ እስኪያቅተኝ ሁሉን ለማሰብ መላው ጠፍቶኝ ልቤም ውስብስብ አይኔ ይሁን ጊዜው እንዲህ የጨሐመው ብርሀን የራቀኝ መች ይሆን ሚነጋው መውደቅ መነሳቱ ይኸው በሰው ጉዞ መች ይመልስና የወሰደ አፍዝዞ የለኝ ምናፍቀው ከአይን የራቀ ከልብም ይርቃል ወዳጄ የምለው ስወድቅ መቼ ያውቃል ማንም ከሌለበት ራቅ ካለው ቦታ እኔው ላይ መልሶ ይጮሃል ዝምታ ሰው እኮ ነው ለሰው መድሀኒቱ ይቀል የለም እንዲህ መተረቱ ያስደንቅ አይደል ራስን አይቶ ማበድ ብቻ ተመኙ እንደ አዲስ መወለድ ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
