ኢትዮጵያዬ
ስሰማው የነበር ትናንትን በድሮ ወይኔ ጉድ አሰኘኝ ዛሬን በዘንድሮ ህልሜስ ህልም ነበር የተዋጣለት መች እረፍት ሰጡን እነ እንሽላሊት ኸረ መላ በይ አገሬ ኢትዮጵያ ሊያጠፉሽ ደርሰው አድገው ባንቺ ጉያ ተከብረሽ እየኖርሽ የለ ቀኝ ግዛት ያንቺው ልጆች ናቸዉ የሆኑብሽ ውጋት ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ላይሆነን መኖሪያ ብሔር እየለዩ መውገር እንደ አህያ ከምንም በላይ ነው የሰው ልጅ አምሳያ ባንድ ጎጆ ጥላ ሳለን በምሶሶ የትኛው ዳኛ ነው ሚለየን ጨርሶ አምሮብን ደማምቀን በሶስቱ ቀለማት በታሪክሽ ዝና ሲደነቁ አገራት ሰው ያለ አገር አገርም የለ ሰው ትርጉም የለሽ ዛቻ ምድራችን ባዶ ነው ሚዛን ቀኗ ርቆ ውስጤን ያስጨነቀው እናት ኢትዮጵያ ድምፅሽ ጠፋኝ የት ነው ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
