ይሁዳ አፈረ
ይሁዳ አፈረ ዲናሩን አብልጦ፤ በክህደት መንገድ ከህሊና በልጦ። ፈጣሪም ጠየቀው ነገሩንም አውቆ፣ አንደበቱ ላላ ልቡ ተሸማቆ። አሁን ያቺ ዲናር አምላኳን እረሰሰታ፣ ክህደት ምንጭ ሆነች ይሁዳን አሳስታ። እልፍ አእላፍ ሆኖ ሲከባት ጥላቻ፣ ምድርን ገዢ ሆነ አንድ ዲናር ብቻ። ይሁዳ በድሎ እራሱን አጠፋ፣ ከይሁዳ በልጠን ለጦር ስንለፋ፣ ሀላፊ ኑሮአችን እኛን ባዩ ጠፋ። እኛው ገዢ ሆነን እኛው እኛው ሆነን ገልጋይ፣ እኛው ፈራጅ ሆነን እኛው ሆነን ሠቃይ፣ ብርስ ገዢ ሆነ ወረቀቱስ ገዳይ። ሠው በፈጠረው ተገዛ እራሱ ፣ ምነው ቢያገናዝብ ቢያስብም ፈረሱ፣ አጥፍቶ መጥፋትን እራስን ቢከሱ፣ ሁሉን ተናጋሪ ሕሊና ነው ልብሱ። ሠው ከሕሊና ብሶ ክህደት ማቅ ለብሶ፨ ገንዘብ አለም ጎርሶ ባዶነት አላብሶ፣ ዘሩ ተከፋፍሎ ምድሩስ ተቆራርሶ፣ ገዢ አድረገው ከግብዙ ብሶ። ጥፍር ገማ ብለን ባንቆርጥ የራስ ስጋ፣ ፈጣሪ ብሩክ ነው ባንከፍልለት ዋጋ፣ የዘመድ ባድ ቆርጠን የዘር መንጋ፣ እኛው ተከፋፍለን በሀይማኖት አልጋ። አንደበት ተዘጋ ልብ ደነደነ፣ ባዶነቱ ገኖ እንዲው የባከነ፣ ጥላቻው ተናግቶ ሀሰቱ ገነነ። እውነት እና ሀሰት ባንድ ሰው ተናጋ፣ ስጋ ባናወጣ ከአንበሳ መንጋጋ፣ በአንድነት እንሙላ ፍቅርን ፍለጋ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
