ብዕሬን አምጡልኝ
ብዕሬን አምጡልኝ ወረቀት አንስቼ መጫሬን ጀመርኩኝ ሳወራው የልወጣ ውስጤ የቀረብኝ ተፍኖ የቆየ ስር የሰደደብኝ .... ወረቀቴ ስሚኝ ላንቺ ላወራ ነው ምንም አድማጭ ባጣ አንቺን አግኝቻለው ውዴ ወረቀቴ ከልብሽ አድምጭኝ ብዙ አላወራም አንዴ ትኩረት ስጭኝ ...... ውስጥ ውስጤን የበላው ለማውራት በዝቶብኝ ልቤ ፍቅር ይዞት ምን ልሁን አስባለኝ የፍቅሩ መዕበል እያወዛወዘውኝ ገና በመለደው ልቤን ደስ አሰኘኝ ..... ለባዘነው ልቤ የሆነው እረፍት ከቃላት ያለፈ ሆነልኝ ትምክት ........ ፍቅርህ እንደወንዝ በውስጤ ፈሰሰ ያለፈው ህይወቴ በደምህ ታደሰ በቃላት የማይገለጥ ግሩም ነው መውደድህ ቀልቤን ሳብከው እና አብዝቼ ፈለኩህ ..... ፍቅርህ ሰላም ሰጠኝ ልቤ በአንተ አረፈ የልቤ ጭንቀቱ በአንዴ ተገፈፈ ልቤ ታምኗል እና በአንተ ፍቅር ሌላው ሌላው ነገር አይምጣብኝ ይቅር ...... ማነው አንተን ከእኔ የሚለይብኝ? መከራ ወይስ ጭንቀት ማጣት ወይስ ስደት ሞት ቢሆን ህይወትም ዝቅታ ቢሆን ከፍታም ማንም አይለየኝም አንተን ከእኔ ይህንን አውቃለሁ በዘመኔ ......... እኔን አሁን ቢይዘኝም ከእርሱ ፍቅር አርሱን ቀድሞ ያዘው አለም ሳይፈጠር ....... ክርሰቶስ ፍቅር ነው ይህንን አውቃለሁ እስከዘላለም በእርሱ እኖራለሁ ........ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ሊለይ ይችላል የትኛውም ቢሆን ዛሬ ተሸንፏል ........ በሮሜ ክፍል ውስጥ ቃሉ እንደሚለው ማንም እንዳይለየኝ ይህን አውቂያለሁ ..... የእኔ ጓደኛዬ ውዷ ወረቀቴ ሀሳቤን እንድፅፍ ሆንሽኝ ረዳቴ ........ ኑሪልኝ ብዕሬ ባለውለታዬ ፍቅሬን አሳወኩት ለጌታዬ
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
