አንድ ናት ሀገሬ
ሀገሬ ሀገሬ የምልሽ በኩራት ስላንቺ ባወራ ተሞልቼ ድፍረት ዜግነትሽ ቢሉኝ ሙሉ ኢትዮጵያዊ የምኖር በደስታ ሆኜ ሰላማዊ ታላቅ ነው እርስትሽ የ እግዚአብሔር ሀገር የፍቅር ተምሳሌት መርጦሻል በክብር የሰው ዘር መገኛ የዱር የ አራዊቱ ላንቺ የዘነበው የ አምላክ ቸርነቱ የሌላውን ባላውቅ ላድንቅሽ በግሌ ከልቧ ሀገር ነሽ የምን ገለመሌ ሀገሬ ስላንቺ ብዙ ብናፍቅም ብቻ ሁኚ ሰላም ተስፋዬ አያልቅም ይራቅ ከልጆችሽ የመከራው ጉዞ አንድነት ይቅረበን ሁሉ ተሰርዞ ጀግኖች አባቶቼ ያወረሱኝ በአደራ ቀን አላት ሀገሬ አትቀርም ተደፍራ ጆሮ የለኝ ሰሚ ተቃራኒ ወሬ አልደራደርም በአንቺ እኮ ነው ክብሬ አንድ ነሽ ኢትዮጵያ ተቀያሪ የለሽ ለመጠራት ያንሳሉ አይደለም ሊተኩሽ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
