ሰው ነኝና
በደሌም ከክምር በላይ የበዛው ልክ የሌለው ጥፋቴም ቅጥ ያጣው ዛሬን አለሁ ብዬ ለነገ ጭለማን ተመኝተው ሰው ነኝና ሰው ነኝና ስሕተቴ ብዙ ነው ይቅር ባይ አምላክ ሰውን የማይጥለው እንደርሱ ቢሆንማ ቅጣቴ ክፉ ነው እውነት ተደፍና በውሸት ተጋርዳ እምነት ተጠቅጥቆ በክሕደት ቀዳዳ ተቆጥሮ የማያልቀው የኔ እዳ በደሌን ሰርዞ ዝም ሲል ወዳጄ አይቶ እንዳላየ አይዞሽ ብሎ ልጄ ሕሊና የራቀኝ ፍቅር ያጣሑኝ ሰው ሰው ነኝና ሰው ነኝና ጥፋቴ ብዙ ነው።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
