አንቺን ያየ ሁሉ ገጣሚ ይሆናል
አንዳንድ ውበት አለ ውበት የማይገልፀው ቆንጆ ይሉት ቋንቋ ስያሜው ያነሰው። አለ አይደል ከስሙ ሚማርክ ቁንጅና ከቃላት የላቀ ከቅኔ የቀና። አንዳንድ ውበት አለ ከሰው የነጠረ 'ካፈር የማይመስል ከመልዓክ ያማረ። ፍፁም ነው እንደዚህ ውበትሽ ፍጥረቱ ድንገት ያየሽ ሁሉ... በቃ ፈላስፋ ነው፣ ቅኔ ነው ህይወቱ ድንገት ያየሽ ሁሉ ገጣሚ ነው እቱ። ለቃል ላንደበቱ መጠን ያጣች ነብሱ በፀጋዬ ቀለም ስንኝ ስትመጥን አይገባውም እሱ እኔም ያልገባኝን ግጥም ለመፃፌ መልክሽ ነው ጥንስሱ። ውበትሽ ሀሺሽ ነው እንከፍ ያባንናል እንቺን ያየ ሁሉ ገጣሚ ይሆናል በደበበ ቀለም ስንኝ ይመጥናል ጠረንሽን ለምዶ ጠረንሽ የራቀው ከራስ ይመንናል። ...ሳይሽ ይሄ ሆነ... የከበበኝ አዚም ድንገት ተበተነ ያሰረኝ ድባቴ ከነፍሴ መነነ ሳይሽ ይሄ ሆነ... ያደረብኝ ቅዠት ከላዬ በነነ። ያገኘሁሽ ጊዜ... ያገኘሁሽ ጊዜ ውበትሽን ሊገልፅ ቋንቋ ተናነሰ ቃል አልባ መገዛት ለልቤ ፈሰሰ ከሰማየ ሰማይ: አንግሳት!!.. የሚል ቃል ለነብሴ ደረሰ ያገኘሁሽ ጊዜ... ህዋስ፣ ጅስሜ ሁሉ ዶርዜኛ ደነሰ ሚገልፀኝ ቃል ጠፋ ቋንቋ ተናነሰ ያገኘሁሽ ጊዜ... ድምፅ አልባ ችክችክታ ለልቤ ደረሰ። ...ሳይሽ ይሄ ሆነ... ደማቅ ወንድነቴ 'ካዳም ዘር ገነነ። ቃል አልባ ቅዱስ ድምፅ ከቃል የተዋበ በጅስም በደሜ ፍቅርሽን ከተበ። አንቺን ያየ ሁሉ ገጣሚ ይሆናል ጠረንሽን ለምዶ ጠረንሽ የራቀው ከራስ ይመንናል የሙሾ ማውረጃ ስንኝ ይመጥናል። ያየሽኝ እንደሆን... ያገኘሽኝ ጊዜ: የአይንሽ ብልጭታ እይታዬን ሲፋ'ጅ አይኖችሽ ዝምድና ጨዋ የልብ ወዳጅ አይኖቼ ግርድና ድፍርስ ፅልመት ቀርዳጅ። የነብሴ ኑዛዜ ከነብስሽ ደርሳለች በድብዝዝ አንደበት ቅኔ ተቀኝታለች 'እግዞ ለውበትሽ...' ምናምን እያለች ፍፁም ያልገባኝን ግጥም ትገጥማለች። አየሽ... አንቺን ያየ ሁሉ ገጣሚ ይሆናል ጠረንሽን ለምዶ ጠረንሽ የራቀው ከራስ ይመንናል የሚቀኘው ቅኔ ቅኔን ይኮንናል ቅዱሳን ያረክሳል፣ ነፋሳት ያፍናል ሳይሽ ይሄ ሆኗል።
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
