ራስን መፍራት
ክብርን አሳንሶ አንገት አቀርቅሮ እንደሌለ አካል ራስን በራስ ቀብሮ ከማን ለማስጣል ነው ራስን ደፍሮ ላም ባልዋለበት አሉ እበት ለቀማ ሳይቋጭ የወጣ በማን ሊያምር ሸማ መፍራትን አይሆነው ከሰዎች መሸሸግ በዝምታ የነጠረ ምላሽን መፈለግ አይደል በቸኮለ ምላስ ባስረዘመ ቃሉን የገደበ ክብሩን አስቀደመ የውስጥን አዳምጦ ለእውነት መወሰን ክፋትን ችላ በል ከየትኛውም ወገን ራስን መፍራት ለራስ መገዛት ነው ራስን መፍራት ራስን ማዳመጥ ነዉ ራስን መፍራት ራስን መውደድ ነው ሌላ ታሪክ አይደል የምትፈለቅቀው መሆን የሚቻለው ባለሙሉ ተስፋ ራስን በመፍራት ሕይወትን ስንገፋ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
