ተው ልቤ
ሀይል ከእኔ ርቆ ጉልበቴ ከድቶኛል ብርቱ የነበረው ልቤም ልብ ይመኛል መዳን ነው ናፍቆቴ ባልልም አሞኛል ደህና ነኝ እያልኩ ሰላሜ ሸሽቶኛል ተው ልቤ!! አድምጥ እራስህን ተከተል ህልምህን ንቃ ለማድመቅ የነገው ቤትህን ፍቅርን ካልክ በልቶ ይክድሃል ደግሞ ወዳጅ ካልክ አኝኮ ይተፋሃል አትፈልግ ምስክር አንተን ባይ ሹመኛ ተቆጠብ ከመጥፎው ለራስህ ሁን ዳኛ እኔን ቢናፍቀኝ ያያያያ ልጅነቴ ጭቃ እያቦካሁ ብቻዬን ማውራቴ እንደዚያ ስቦርቅ በትንሿ ልቤ አሁን ማን ሊሰጠኝ ሁሉንም ተርቤ ተው ልቤ!! ተው ልቤ እያልኩ የማጨናንቀው አቅም የለኝ ሁሉን ችዬ የምርቀው ተመኘሁ ምን አለ እንዳዲስ ብፈጠር ሀሳብ ከሌለበት ወይ ልጅ ሆኜ ብቀር እውነትን የያዘው አይንና ምላሴ የሚቀድመኝ እንባ ብሶተኛው መልሴ በሰው አሉባልታ ወድቄ ብገኝም አምላክ ያንሳኝ እንጂ ክፉ አይወጣኝም። ባዝን ልቤ ሆኖ የሸክላ ስባሪ ቢከብደኝ ቢጨንቀኝ ሰጠሁ ለፈጣሪ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
