እመነኝ
ባየኸው የውስጤን የልቤን ትርታ ሳወራህ በድፍረት ሳለይ ስዓት ቦታ ቢመስልህ የኔ እውነት ላንተ ሁሉም ውሸት ታድያ እንድታምነኝ ሕይወት መጥፋት አለበት ቃሌ ካልማረከህ ቀልብህን ካልገዛው እመነኝ ግድ የለም ተግባሬ ፈራጅ ነው ደንዳናው ልቤን በፍቅርህ አቅልጠህ የረጋው ሀሳቤን እንደ እሳት ቆስቁሰህ ያኔ በአንድ እይታ ወድሻለው ብለህ ምነው አሁን የኔን ለማመን ከበደህ የሚደምቀው ፍቅርህ እለት ከእለት መቼም የማልተውህ በህይወት ሰንሰለት እያደር ይብሳል ፍቅርህ ለእኔ እንግዳ መዓዛህ ልዩ ነው የኔ ጽጌረዳ አንተን የመሰለህ የዋዛ ፈዛዛ እርስት ሆኖኛል ልቤን እየገዛ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
