ይቀጥላል
ምድር ተከፈለች ተሠባብራ ለሁለት፣ ጎሳ ተደረገች በአነሰድምታ ግርምት፣ ሠማይ እና ምድር ተፈራርቆ ህይወት። ጸሀይ ደበዘዘች ብርሀኗን አጣች፣ ጨአቃ ፈዘዘች መነሰገድ ቦታ ቀረች፣ ጨለማ ገዥ ሆነች አለምን አጠፋች። ጀንበር አዘቅዝቃ ማቅ ስቃይ ለብሳ፣ አለም እርቃን ሆና ስቃይ ጉድባ ጎርሳ። ቀን ለሊት ታጦ በባዶ ተውጦ፣ ከሞት ጋር ፍጥጫ ከሕይወት አምልጦ፣ ወንዞችም አነሱ በደም ቅልመት ሠምጦ፣ ላያመልጥ መሯሯጥ ለሞት እጁን ሠጦ። ተራሮች ተናዱ ቅንጣት ሆነው ጠፉ፣ በረዶች እንደ ንፋስ ተነው ግን አለፉ። ሲያሳየኝ ነበረ የቤቴ ዳርዳርታ፣ ተከፍሎ ሲያሳየኝ የቤቴ ውስጥ ቦታ። መአቱን ሲያሳየኝ የቤቴ መስታወት፣ ሀሳቤ ውስጥ ሆኖ አለምን ሲከፍሉት።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
