እኔነቴ
ሀ ብዬ የጀመርኩት የሕይወቴ ምዕራፍ ስወድቅ ስነሳ ከቤቴ ደጅ አፍ ቆረቆረኝ ሳልል ስጎተት በዳዴ መቦረቅ ያምረኛል ሳይርበው ሆዴ ይህ ሁሉ አይመለስ ተለውጧል አንዴ አሁን ግን ለየሁኝ ከእንክርዳድ ስንዴ የሰው ልጅ እንዲህ ነው እያደር ይበስላል ማንነቱ እንጂ ሕይወት ይቀጥላል እኔነቴስ የታል ከወዴት ላግኘው አለም ብልሹ ናት ሁሉንም ተመኘው ሞን አይነት ዘመን ነዉ ራስን የሚያስጠላ ጠጅ እያስወደደ ከማር የሚያጣላ ተይ በሉኝ ሰዎች ኧረ ስጡኝ መላ ንፋስም የሌለው ልክ እንደ ደመና ጨለማ ሆነብኝ የሕይወት ጎዳና የሕይወቴ ሙሉ ትንሽ ደስታ ለኔ ስከፋም እንደዚያው ይበዛል ሀዘኔ እሹሩሩ እንዳልተባልኩ በእናት ባባቴ እጅ አለምስ ክፉ ናት ለማንም የማትበጅ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
