እኔ ላንተ
ምን አሉህ ስለኔ ነገሩህ አቶድህም ብለው ብዙ ጠረጠሩ አንተ እኮ አታፍርም ታምናቸው ይሆናል ስቅም ሲለኝ ነበር ሳታማኝ ይቀራል እኔን ያላዳመጥክ እወድሀለሁ ስልህ ቅንጣት አልመሰለህ አፈቀርኩህ ብልህ ባስብም ባወራ ባልምም ስላንተ ከእኔ በላይ ልቤም ሚታመነው ላንተ ወድጄ መሰለህ ቀን መሽቶ እስኪነጋ ስላንተ ማስበው ይህ ልቤ ነው እንጂ አንተን አንተን ብሎ ሸፍቶ የቀረው ብርድ ያንቀጠቀጠው ጋቢውን ደራርቦ ያንተን ፍቅር ሲያገኝ ሊያቀልጥ በረዶ ውሸት ነው እንዳልል አይኔ ያሳብቃል እንባ እያቀረረ ውስጤ ይታወካል አመት አስቆጠረ ጊዜ የማይለውጠው ልቤ ባሰበህ ቁጥር ላንተ የሚመታው ኸረ ምን አለብህ ምን ከምን አየኸው እኔ በቆምኩበት ቆመህ ካላየኸው እህ ብሎ ሰሚ የውስጤን አዳማጭ የት አገኝ ይሆናል ለየትኛው ሸንጎ ለየትኛው ዳኛስ ብነግር ያምርብኛል ቻይ አስፋልት ሆንኩልህ ሁሉን የሚያሳልፍ ዃላ እንዳይቆጭህ በልቤ ላይ እረፍ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
