ለማታውቂኝ
ተሸነፍ....ኩልሽ ተብ...ረከ...ረኩ...ኝ እኮ እሷን ላፈቅር?! ያኔ እንዳላልኩኝ አንቺን መውደዴን ፈራሁ ልነግርሽ አይሆን ብትይ ነው ምን ታመጫለሽ? ደግሞ 'ፎክራለሁ በሌለሽበት ባይገርምሽ እቴ አንቺን ያየው 'ለት 'ምናገርበት የለኝ አንደበት ይህ የሚያወራው ይዘጋል ልሣኔ የሌላ እንጂ አይመስለኝ የኔ ይኸውልሽ........ በቀደም 'ለት እሑድ እቃ ልገዛ ሱቅ ሄድኩኝና ውስጤ "አይዞህ አትፍራ አጠገቧ ቁም መውደድህን ንገር አትበላት ዝም ለስም ነው እንዴ ወንድ አይደለህም? ምን ይመጣል ብዬ ከጎንሽ ቆምኩና ማነው ደሞ ይኼ እኔን ለማየት ብትዪ ቀና ሰማይ እንደ ቁና ተደፋብኝና ያ ደነዝ ባለ ሱቅ "ምን ልስጥህ"?ብሎ አንቺን ከማየት ሁኔታዬን አይቶ ደግሞም ግራ ገብቶት እየገለፈጠ ጥቂት ሲያናጥበኝ በንዴት ውስጥ ሆኜ የምለው ቢጠፋኝ ፋርማሲ ይመስል'ፓርስታሞል' አልኩኝ አየሽ እቴዋዬ የኔ ተወዳጅ ዛሬማ ቱ...ብዬ 'ነግራታለሁ ብልም ፊቴ ስትደቀኝ ብደነባበርም የፈለግሽውን በይ ማፍቀሬን አልተውም ብጠይቅሽ እንኳን 'ወድሻለሁ ብልሽ "ሂድ!"ብትዪኝ እንጂ አይሆንም ነው እንጂ መንግሥት አታመጪም © Abraham Alemayehu (ልቤን ለከፈልሽው ላንቺ) ተፃፈ 17/03/16 5:15 pm
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
