አንቺ ሴት
ውበትሽ ልዩ ነው እንደ ፀሀይ ጮራ ድንቅ ነው ችሎታሽ ከሩቅ የሚጣራ ሀሳብሽ የራቀ ልብሽ ነው ተራራ መች ያልፍና ሁሌም ስምሽ ሳይጠራ የጨለማ ፋኖስ የሁሉ ምሣሌ የጥንካሬ ምንጭ የኔ አንገተ ብርሌ እንዲ ናት እንዲያ ናት በግምት ይላሉ ስላንቺ ሳያውቁ ብዙዎች ተጣሉ ጠቆረች ከሳች ረዘመች ቃላት ደረደሩ አንቺን ላይመጥንሽ ብዙ ተናገሩ ማን ይወዳደራል አንቺ እኮ ጀግና ነሽ ደስታ ፍቅር ፅናት ሁሉንም የታደልሽ እናት ቢሉ አባት እህት ወንድም ሳይቀር ሁሉንም የተካሽ እስኪ የማን ጎበዝ ችሎ ይወዳደርሽ የአምላክ ፍቃድ ሆኖ ህይወትን የዘራሽ ሰንቱ ቢታጨድ ነው ይህን ሁሉ የታደልሽ ምክንያትሽ ቢበዛ ሁሉም አከበረሽ ሲከፋሽ አሎድም ፈገግታ አይለይሽ።
Ad
Poetry Books 50% Off
Bestselling collections from top poets
Shop Now →
